ሉና ሶፍትዌርን በነጻ ይሞክሩ!

ሲመዘገቡ በነጻ ለ40 ቀን መጠቀም ይችላሉ። በቀላልሉ አውርደው ጭነው ይሞክሩ።

ራስ-ሰር የሆነና ሰራተኞች በተቀጠሩበት መስሪያ ቤት ያላቸውን ፋይናንሺያል ሪከርድ የሚያስተዳድር ሶፍትዌር ሲሆን አስልቶ አስፈላጊ የሆኑትን ሪፖርቶች የሚያዘጋጅ የተቀናጀ ሲስተም ነው። እንደ ሀገራችን የገቢዎች ህግ መሰረት እነኚህን ሪፖርቶች ሲያዘጋጅ የገቢዎች ቢሮ ያዘጋጀውን ሪፖርት ማድረጊያ ቅፅ በመጠቀምና ፍፁም ተመሳሳይ በማድረግ ጭምር ነው። አነስተኛ ፣ ትላልቅ ፣ ነባር እንዲሁም አዳዲስ ድርጅቶች ይህ የተቀላጠፈ የደሞዝ ማስተዳደሪያ ስራዓት ያስፈልጋቸዋል። አዲስ ድርጅት የሚመሰርቱ ግለሰቦችም ይሁኑ ማህበራት ከሰራተኞች ደሞዝ ጋር ተያይዞ ስላሉ አሰራሮች ግንዛቤው ከሌላቸው ይህንን ሶፍትዌር በመጠቀም ያለባቸውን የተወሳሰበ ስራ ማቅለል ይችላሉ።